
በ2026 የዩቲዩብ ቻናልዎን የሚያሳድጉበት ምስጢር! TubeBuddy፣ VidIQ ወይስ Viewstats - ለእርስዎ የትኛው ይበጃል? ከA/B testing እስከ AI የቪዲዮ ሀሳቦች፣ እንዲሁም የተፎካካሪዎችን ስልት እስከ መሰለል ድረስ ያሉት አስገራሚ ጥቅሞች በዚህ ጦማር ውስጥ ቀርበዋል። ከታች ያለውን ያንብቡና የቪዲዮዎችዎን እይታ እና ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ያሳድጉ!
5 min read
TubeBuddy vs VidIQ vs Viewstats የዩቲዩብ ቻናላችሁን ማሳደግ ከፈለጋችሁ ስለ TubeBuddy፣ VidIQ እና Viewstats ማወቅ ይጠበቅባችኋል። እነዚህ ሶስት በብሮውዘር (browser) ላይ የሚሰሩ መገልገያዎች (tools)፣ በእውነተኛ መረጃ (data) ላይ ተመስርተው ማደግ ለሚፈልጉ ክሬኤተሮች ዋነኛ ምርጫዎች ነው። ነገር ግን ሶስቱም የተሰሩት በተመሳሳይ መንገድ አይደለም፤ የተሳሳተውን መምረጥ ግን ጊዜያችሁን፣ ገንዘባችሁን እና የቻናላችሁን እድገት ሊያሳጣችሁ ይችላል።
በዚህ ጦማር ውስጥ፣ እያንዳንዱ መገልገያ ምን አይነት አገልግሎት እንደሚሰጥ፣ ምን ላይ የተሻለ እንደሆነ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ አሁን ባላችሁበት ደረጃ ለቻናላችሁ የትኛው የተሻለ እንደሆነ እንመለከታለን። እነዚህ መገልገያዎች (Tools) ምንድን ናቸው? ክሬኤተሮችስ ለምን ይጠቀሟቸዋል? እነዚህ መገልገያዎች (Tools) ከማወዳደራችን በፊት፣ እያንዳንዱ መገልገያ የትኛውን ችግር ለመፍታት እንደተሰራ መረዳቱ አስፈላጊ ነው።
TubeBuddy፦ በቀጥታ በዩቲዩብ ስቱዲዮ (YouTube Studio) ውስጥ የሚሰራ የብሮውዘር ኤክስቴንሽን (browser extension) ነው። መረጃዎችን በቀጥታ በዩቲዩብ ገጽ ላይ ስለሚያሳይ፣ ሌላ ታብ (tab) መክፈት ሳያስፈልጋችሁ የኪዎርድ ምርምር (keyword research)፣ የ SEO ውጤቶች፣ የታግ (tag) ጥቆማዎች፣ የ A/B ሙከራዎች እና bulk editing ለማድረግ ያስችላል። በዩቲዩብ እውቅና የተሰጠው ሲሆን በዘርፉ ላይ ከአስር ዓመታት በላይ ቆይቷል።
VidIQ፦ በተመሳሳይ እንደ ብሮውዘር ኤክስቴንሽን የሚሰራ ቢሆንም፣ ይበልጥ ትኩረት የሚያደርገው በይዘት ስትራቴጂ (content strategy) እና በ AI (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የታገዙ ሀሳቦችን ማፍለቅ ላይ ነው። ዋና ጥንካሬው ቪዲዮ መቅረጽ ከመጀመራችሁ በፊት ምን መስራት እንዳለባችሁ ለመወሰን መርዳቱ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው በኪዎርድ (Keyword) መረጃዎች፣ በተፎካካሪዎች ክትትል (Competitors Analysis)፣ በየቀኑ በ AI በሚመነጩ የቪዲዮ ሀሳቦች እና አዳዲስ ዝንባሌዎች (trends) ጥቆማዎች ነው።
Viewstats፦ ሙሉ በሙሉ የተለየ አቅጣጫ ይከተላል። በታህሳስ 2023 በጂሚ ዶናልድሰን (MrBeast) እና ቻኪ አፕልቢ (Chucky Appleby) በጋራ የተመሰረተው ይህ መገልገያ፣ የቀጥታ ሰዓት አናሊቲክስ (real-time analytics) እና የተፎካካሪዎችን መረጃ በመሰብሰብ ላይ ያተኮረ ነው። ታዋቂነቱ በየቀኑ ከአብዛኞቹ ተፎካካሪዎቹ በበለጠ ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃ መተንተን መቻሉ ነው፤ ይህም በዩቲዩብ ታሪክ ትልቁ ከሚባለው ቻናል ጀርባ ያለውን ስትራቴጂ መሰረት ያደረገ እይታን ይሰጣል።
TubeBuddy፦ የኪዎርድ መፈለጊያው (Keyword Explorer) ከዩቲዩብ ገጽ ጋር በደንብ የተዋሃደ ስለሆነ፣ ስራችሁን ሳታቋርጡ ለመመርመር እና ለማስተካከል ቀላል ያደርገዋል። በዩቲዩብ ስቱዲዮ ውስጥ እየሰራችሁ አጠቃላይ የኪዎርድ ውጤትን፣ የትሬንድ መረጃዎችን፣ ተዛማጅ ፍለጋዎችን እና የታግ ጥቆማዎችን በቀላሉ ማየት ትችላላችሁ።
VidIQ፦ የኪዎርድ መረጃው ወቅታዊ ዝንባሌዎችን (trends) በመለየት ረገድ የተሻለ እንደሆነ በሰፊው ይታመናል። አንድ ኪዎርድ ስታስገቡ፣ VidIQ አጠቃላይ ውጤቱን ከፍለጋ መጠን (search volume)፣ ከተዛማጅነት ውጤት እና ከተወዳዳሪነት ደረጃ ጋር ያሳያል። በፍለጋ መጠን መሰረት መደርደር ስለሚቻል፣ የትኛውን ቀድማችሁ መስራት እንዳለባችሁ ለመለየት ይረዳል። በፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ርዕሶችን ለሚሰሩ ክሬኤተሮች፣ የ VidIQ የኪዎርድ መገልገያ ይበልጥ ተግባራዊ ምርጫ ነው።
Viewstats፦ በዋናነት ለኪዎርድ ምርምር የተሰራ አይደለም። ጥንካሬው አስቀድሞ ውጤታማ እየሆነ ያለውን ነገር መከታተል ላይ ነው። ለምሳሌ ከቻናላቸው አማካይ እይታ በላይ የሆኑ "Outlier" ቪዲዮዎችን ማግኘት፣ ቫይራል የሆኑ ትሬንዶችን መለየት፣ እና የእናንተን ተምብኔል (thumbnail) እና የይዘት ስትራቴጂ ከተፎካካሪዎች ጋር ማወዳደር ነው።
ማጠቃለያ፡ ለኪዎርድ ምርምር ጥልቀት VidIQ የተሻለ ሲሆን፤ TubeBuddy በስራ ፍሰት ውህደት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል። Viewstats ግን ለኪዎርድ ምርምር የሚሆን መገልገያ አይደለም።
TubeBuddy፦ ጠንካራ የቪዲዮ አናሊቲክስ ማጠቃለያ ማለትም አጠቃላይ እይታዎች፣ አስተያየቶች፣ ላይኮች፣ ጥቅም ላይ የዋሉ ታጎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ እይታዎች እና የቻናል ደረጃ መለኪያዎችን ይሰጣል። በተለይም የ SEO ውጤት ማሳያ ሰሌዳው (scorecard) እያንዳንዱን ቪዲዮ ለመገምገም እና የት ላይ መሻሻል እንዳለበት በትክክል ለማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው።
VidIQ፦ በየሰዓቱ ያለውን የእይታ መጠን (Views Per Hour - VPH) መከታተያ ያቀርባል፤ ይህም ቪዲዮዎቻችሁ ከተለቀቁ በኋላ ባሉት ሰዓታት ውስጥ የእናንተም ሆነ የተፎካካሪዎቻችሁ ቪዲዮዎች ምን ያህል ፍጥነት እያገኙ እንደሆነ ያሳያል። ይህ ቀድሞ የሚመጣ ምልክት ቪዲዮው እየታየ መሆኑን ወይም የርዕስ እና ተምብኔል ማስተካከያ እንደሚያስፈልገው ለመገመት በእጅጉ ይጠቅማል።
Viewstats፦ በአናሊቲክስ ረገድ በጣም ጥልቅ መረጃ ይሰጣል። ፕላትፎርሙ የተገነባው በዩቲዩብ ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ በሰፊው ለማሳየት ነው። ይህም ዕለታዊ ስታቲስቲክስ፣ የቻናል እድገት አቅጣጫዎች፣ ግምታዊ ገቢዎች (estimated earnings) እና ከሌሎች ተመሳሳይ ቻናሎች ጋር የሚደረጉ የንፅፅር መለኪያዎችን ያካትታል። በተለይ "Outlier detection" (ከመደበኛው ውጪ የወጡ ቪዲዮዎችን መለየት) ባህሪው፣ ከተጠበቀው በላይ እጅግ ከፍተኛ እይታ ያገኙ ቪዲዮዎችን ነጥሎ ያሳያል፤ ይህም የውጤታማ ቪዲዮዎችን ስልት መልሶ ለመስራት (reverse-engineering) በዋጋ የማይተመን ነው።
ማጠቃለያ፡
በአናሊቲክስ ጥልቀት እና በተወዳዳሪዎች ክትትል (Competitors Analysis) Viewstats ይመራል።
የ VidIQ የ VPH መከታተያ ደግሞ የቀጥታ ሰዓት አፈጻጸምን (real-time performance) ለመከታተል ምርጥ ነው።
TubeBuddy መሰረታዊ ነገሮችን በጥሩ ሁኔታ ይሸፍናል።
ይህ የ TubeBuddy ልዩ ባህሪ ሲሆን በጣም ወሳኝ ጥቅሙ ነው። TubeBuddy ተምብኔሎችን፣ ርዕሶችን፣ መግለጫዎችን (descriptions) እና ታጎችን በተለቀቁ ቪዲዮዎች ላይ በእውነተኛ መለኪያዎች (እንደ CTR እና View duration) ላይ በመመስረት A/B Testing እንድታደርጉ ይፈቅድልዎታል። ነገር ግን VidIQ እና Viewstats ይህንን መሰል ባህሪ ወይም አገልግሎት የላቸውም። በመረጃ ላይ የተመሰረተ የተምብኔል እና የርዕስ ሙከራ ለእናንተ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ከሆነ፣ ይህንን የሚያቀርበው ብቸኛው መገልገያ (Tools) TubeBuddy ነው።
VidIQ፦ በዚህ ረገድ በጣም ጠንካራው ነው። የእሱ "AI Daily Ideas" ባህሪ ለቻናላችሁ ዘርፍ (niche) የተበጁ ያልተገደቡ የቪዲዮ ርዕስ ጥቆማዎችን ያመነጫል፤ እንዲሁም ሰዎች በእርግጥ እነዚያን ርዕሶች እየፈለጉ መሆኑን ለማረጋገጥ ከፍላጎት መረጃ (demand data) ጋር አያይዞ ያቀርባል።
TubeBuddy፦ የ AI ርዕስ እና ታምብነይል ማመንጫዎችን ያካተተ ቢሆንም፣ አብዛኛዎቹ ተቺዎች ከ VidIQ የ AI ጥቅል ጋር ሲነጻጸር ውህደቱ ያነሰ እና ይበልጥ የተለመደ (generic) እንደሆነ ይገልጻሉ። የ TubeBuddy አካሄድ የክሬኤተሩን የስራ ፍሰት ማገዝ እንጂ ሀሳብ ማፍለቅን መተካት አይደለም፤ ምን መስራት እንደሚፈልጉ አስቀድመው እንደሚያውቁ ያስባል።
Viewstats፦ ራሱን እንደ AI ሀሳብ ማፍለቂያ ፕላትፎርም ባያደርግም፣ የ "Outlier detection" እና የትሬንድ መለያ መገልገያዎቹ የዩቲዩብ አልጎሪዝም በአሁኑ ጊዜ በእናንተ የስራ ዘርፍ ውስጥ ለምን ድጋፍ እየሰጠ እንደሆነ በማሳየት ተመሳሳይ ዓላማ ያገለግላል።
ማጠቃለያ፡ በ AI የታገዘ የይዘት እቅድ ማውጣት ላይ VidIQ የተሻል ሲሆን TubeBuddy እና Viewstats በዚህ ዘርፍ የተለየ ዓላማ ነው የሚያገለግሉት።
አንድ ወጥ የሆነ "ምርጥ" የዩቲዩብ መገልገያ የለም። ምርጫው የሚወሰነው በክሬኤተርነት ጉዞዎ ላይ ባሉበት ደረጃ እና የትኞቹን ለማሻሻል እየሞከሩት ባለው ነገር ላይ ነው። ገና እየጀመሩ ከሆነ፣ TubeBuddy Pro ምርጡን የመግቢያ ደረጃ ዋጋ ያቀርባል፤ የ VidIQ ነፃ እቅድ ደግሞ ምንም ገንዘብ ሳያወጡ የኪዎርድ ሀሳቦችን ለመገምገም በቂ ጥንካሬ አለው። Viewstats መመልከቱ ጠቃሚ ቢሆንም፣ ቻናላችሁ ወጥ የሆነ ይዘት ማምረት እስኪጀምር እና ጠንካራ የተፎካካሪ መረጃ እስካላስፈለጋችሁ መጠቀሙ እምብዛም ላያስፈልግ ይችላል።
ቻናላችሁ እያደገ ሲሄድ፣ እነዚህን መገልገያዎች (Tools) ማለትም VidIQን ምን እንደሚሰሩ ለማወቅ፣ TubeBuddyን እንዴት እንደሚያስተካክሉት ለመወሰን፣ እና Viewstatsን ደግሞ የተፎካካሪዎችን ሁኔታ ለመረዳት መጠቀም እጅግ አስፈላጊ እና የጎለመሱ ተጠቃሚዎች (power-user) ምርጫ ነው። ነገር ግን በዋነኝነት ማስታወስ የሚገባን እነዚህ መገልገያዎች (Tools) ብቻቸውን ቻናላችሁን አያሳድጉትም። ነገር ግን የተሻለ ይዘት (Content) አቀራረብ ካላችሁ ቻናላችሁ የበልጥ እንዲያድግ ያግዙዋችዋል።