Banner image for Yematawerk Lema at Geyesse Grass Land BMNP

የዌብ ሸለቆ ትዝታዬ [Memories of the Web Valley]

የዌብ ሸለቆ ከባሌ ተራሮች በሚመነጨው የዌብ ወንዝ፣ በጀምበር መጥለቅ ውበቱ እና በሜዳው ላይ በሚታዩት በርካታ ዝንጀሮዎች የሚታወቅ ማራኪ የተፈጥሮ ስፍራ ነው። ይህ ወንዝ ከደንቃ ወንዝ ጋር ከተቀላቀለ በኋላ 130 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዞ በኢትዮጵያ ረጅሙ የሶፉመር ዋሻ ውስጥ ያቋርጣል። በተጨማሪም በዚሁ የሸለቆው ወንዝ ውስጥ ከኬንያ የመጡና ለመብል ምቹ የሆኑት "ብሮውን ትሮት" እና "ሬምቦ" የተባሉ ሁለት የአሳ ዝርያዎች ይገኛሉ።

1 min read

ጀበር ስጠልቅ እዚህ ስፍራ ተቀምጦ እንደ መመልከት ሚያስደስት ነገር አላጋጠመኝም። ያችን ውብ ጀምበር ለመጥለቅ ስትዳዳ፣ ባላገሩ ወደቤቱ ሲያዘግም፣ ሜዳውን በአፍታ በዝንጀሮዎች ሲሞላ እና በዛ ላይ የነዛ ውብ ዝንጀሮዎች ትርኢት መመልከት መቻል ነብሴ በሃሴት እንድትሞላ ያደርጋታል።

ወደ ባሌ ስሄድ ይህንን ስፍራ መቃኘት ለ'ኔ እጅግ የቅርብ ዘመዴን ሄዶ እንደ መጠየቅ(መጎብኘት) ነው። ደሞ የአያቴ እርሻ በፎቶግራፉ ላይ ካለው ስፍራ ትንሽ ራቅ ብሎ በዚው የወዝ ዳርቻ መገኘቱ ልብ ይባል።

ይህ ወንዝ የዌብ ወንዝ ይባላል። ከባሌ ተራሮች አናት ላይ ከሚመነጩ ወንዞች አንዱ ነው።

በግምት ከተቀመጥኩበት 100 ሜትር ርቀት ላይ ይህ የዌብ ወንዝ ከደንቃ ወንዝ ጋር ተገናኝቶ 130 ኪሎ ሜትር ከተጓዘ በኃላ በኢትዮጵያ ረጅሙ ዋሻ በሆነውን የሶፉመር ዋሻ ውስጥ ያቋርጣል(ይጓዛል)።

በዚኛው የወንዙ አካል ሁለት የአሳ ዝርያወች የሚገኙ ሲሆን፤ እነሱም ብሮውን ትሮት (Brown Trout) እና ሬምቦ (Rainbowfish) ናቸው። እኒህ አሳዎች ከኬንያ የመጡና ለመብል ምቹ የሆኑ እነደሆነ ይነገራል።

ስፍራ: የዌብ ሸለቆ (Web valley)
ባሌ፣ ኦሮሚያ
ኢትዮጵያ

Reach Out

The Latest Blogs